• tell a frined
 • Welcome, Guest. Please login or register.
  August 28, 2016, 07:02:46 AM

  Login with username, password and session length
  Search:     Advanced search
  Home Help Search Login Register
  +  My Community
  |-+  public
  | |-+  ልዩልዩ (Moderator: *gofasefer*)
  | | |-+  መዝሙር
  « previous next »
  Pages: [1] 2 3 ... 12 Print
  Author Topic: መዝሙር  (Read 27841 times)
  reality
  Jr. Member
  **
  Posts: 8


  View Profile Email
  መዝሙር
  « on: May 09, 2007, 09:00:40 AM »

   ኢየሱስ አዜምልሀለሁ

  1.በጨነቀኝ ጊዜ በስምህ ለምኜ
   አምላኬ ስጠራህ አንተን ተማምኜ
   ጩሀቴ በፊትህ ወደ ጆሮህ ደርሶ
   ሰላም ሰተሀኛል ሁሉም ተመልሶ

   ኢየሱስ ዘምርልሀለሁ ከልቤ
   አዘምልሀለሁ ከልቤ
   በስምህ መች አፍሬ አዉቅለሁ ታምኜ
   እዚህ ደርሻለሁ

  2.ምናለ በስምህ እኔ ያልተቀበልኩት
   ደግሞም ተማምኜ በስምህ ያላለፍኩት
   ነፍሴ ታውቅሀለች ታከብርሀለች
   ክብር ሁሉ ላንተ ይሁን እያለች

  3.ስወጣም ስገባ ዘወትር ጠባቂዬ
   ከስምህ በስተቀር ምን አለኝ ጌታዬ
   በሰማይ በምድር ሁሉን ለሚገዛው
   ለታላቁ ስምህ ምስጋና ይድረሰው

  4.በህይወቴ ዘመን ተስፋ ማደርገው
   ለጥያቀዬ መልስ ኢየሱስ ስምህ ነው
   ለትውልድ ለወገን ለሁሉ የማወርሰው
   ዘላለም ንዋሪውን ስምህን ብቻ ነው

  የጣኦታትን ስም

   የጣኦታትን ስም ከምድር ያጠፋል
   ምሽግን ያፈርሳል ምርኮን ዪመልሳል
   እግዚአብሄር ተዋጊ ነው
   ዛሬም ያሽንፋል ዛሬም ድል ያደርጋል
   አሽናፊ ነው አሽናፊ ነው
   እግዚአብሄር ተዋጊ ነው

   
  1.በነቢያት በሀዋሪያት ዘመን እንደሰራው
   እኛም እናያለን እርሱ ጊዜ አይሽረው
   የአማልክትን ስም ከምድር ያጠፋል
   ሀያሉ እግዚአብሄር ከፍ ከፍ ከፍ ይላል

  2.በዲያቢሎስ ወጥመድ የታሰሩ ሁሉ
   በጣኦት አምልኮ ነፍሳቸው የዛሉ
   በሀይሉ ተፈተው ወደርሱ ይመጣሉ
   በአንድነት የሱስን ብቻ ያነግሳሉ

  3.ሀይል አለው ኢየሱስ የሆነ ሁሉን ቻይ
   ስሙ የከበረ ከስም ሁሉ በላይ
   የሚመስለው ማነው በምድር በሰማይ
   ይሰራል ኢየሱስ ከቶ ማነው ከልካይ

  4.ቃል ኪዳኑ የፀና አምላክ ነው ዘላለም
   ሰማይ ምድር ቢያልፉም ቃሉ ግን አያልፍም
   በወደደን በእርሱ ድል እናገኛለን
   እኛም ከአሽናፊዎች በላይ እንበልጣለን
  Logged
  reality
  Jr. Member
  **
  Posts: 8


  View Profile Email
  Re: የኦስሎ ኮንፈረንስ መዝሙሮች
  « Reply #1 on: July 10, 2007, 11:54:54 AM »

   ኢየሱሴ ባንተ ነው ብርታቴ

  ሰምቼም አላውቅም ባይኔም አላየሁም
  በዉኔ ጌታ አላውቅ ያለምንም አጥንት
  እኔንም ጌታ የሱስ ባታጠነክረኝ
  የቅጠል ኮሽታዉ ገደል በከተተኝ

  የሱሴ የሱሴ የሱሴ ነህ እኮ አጥንቴ
  እኔስ ባንተ ነው ብርታቴ
  እኔስ ባንተ ነው  ድፍረቴ

  ኢየሱስ አንተ እኮ የሌለኸው ሰው
  እንክዋን ሌላ ቀርቶ ይፈራል ጥላውን
  እኔ ግን በመሆኔ የሱስ ያንተ ልጅ
  ኮራ ብዬ አልፋለሁ በጠላቴ ደጅ

  መኩሪያዬ መኩሪያዬ ሆነኸኝ
  ዪሀው ዛሬንም አለሁኝ
  ሞገሴ ሞገሴ ሆነኸኝ
  ዪኸው ዛሬንም አለሁኝ

  ለኔ ደስታ ሚሰጥ ነፍሴን የሚያረካ
  ኑሮ ቤት አይደለም የእውቀቴ ጉዞ
  እንዲሁ በባዶ ምንም ሳይኖረኝ
  አንተ ስላለኸኝ ሙሉ ደስታ አለኝ

  ደስታዬ ደስታዬ ሆነኸኝ
  ይኸው ዛሬንም አለሁኝ
  ሰላሜ ሰላሜ ሆነኸኝ
  ይኸው ዛሬንም አለሁኝ

   የሱሴ የሱሴ የሱሴ ነህ እኮ አጥንቴ
   እኔስ ባንተ ነው ድፍረቴ

  ዛሬ በጠላት ፊት ቆሜ ምግዋደደው
  ካንተ የተነሳ ስለበረታሁ ነው
  ጨካኝ አደረከው ልቤን ኢየሱሴ
  ባንተ ተደግፋ ጠነከረች ነፍሴ

  ምርኩዜ ምርኩዜ ሆነኸኝ
  ይኸው ዛሬንም አለሁኝ
  ድጋፌ ድጋፌ ሆነኸኝ
  ይኸው ዛሬንም አለሁኝ
  ብርታቴ ብርታቴ ሆነኸኝ
  ይኸው ዛሬንም አለሁኝ
  Logged
  reality
  Jr. Member
  **
  Posts: 8


  View Profile Email
  Re: መዝሙር
  « Reply #2 on: February 02, 2008, 10:59:57 AM »

  በእምነት ልኑር ከየሱስ ጋራ
  ተማምኜ በታላቅ ፍቅሩ
  ተጠልዬ በፍቅሩ ክንፍ ስር
  በእምነት ልኑር ምንም ሳልፈራ
  Logged
  reality
  Jr. Member
  **
  Posts: 8


  View Profile Email
  Re: መዝሙር
  « Reply #3 on: February 02, 2008, 04:58:53 PM »

  ፃድቅ በእምነት ይኖራል
  ባምላኩ ተስፋ ያደርጋል
  አልመለስም ወደ ሁዋላ
  የሱስ አልሻም ካንተ ሌላ
  እኖራለሁ በእቅፍህ እኖራለሁ
  እኖራለሁ በእቅፍህ እኖራለሁ

  የሱስ ካንተ ጋራ ሸለቆ ተራራ
  ዳገት ቁልቁለቱ ምንም አያስፈራ
  Logged
  reality
  Jr. Member
  **
  Posts: 8


  View Profile Email
  Re: መዝሙር
  « Reply #4 on: February 10, 2008, 03:21:35 AM »

  የታለ ፅድቄ የሚቆጠርልኝ
  ወደየሱስ ፊት እኔን የሚያቀርበኝ
  ግን አንድ ነገር አለኝ ምህረቱ
  የምታመንበት በየለቱ
  ስለዚህ ነው ደስ የሚለኝ
  Logged
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>መድሀኒቴን አየዋለሁ
  « Reply #5 on: January 02, 2012, 05:38:46 AM »

                                   መድሀኒቴን አየዋለሁ


  1. መድሀኒቴን አየዋለሁ አይኖቼ ተከፍተውል   
  በደሙና በስሙ ስላነፃኝ
  ፍፁም ህይወት አሁን አለኝ በሞቱ ፈወሰኝ
  አሮጌው ልማድ ከህይወቴ ጠፍቶዋል::

  አምላኬን ላመስግን ስሙንም ልወድስ
  ስላፈቀረኝ በመስቀል ተሰቅሎ ሀሌሉያ
  በህይወቴ ዘመን ሁሉ የሱሴን ልክተል
  ለአለም ህዝቦች የፍቅሩን ወንጌል ልግለፅ

  2.የህይወት ብርሀን የሆነውን አምላኤን አገኘሁ
  ስሙ የሱስ ነው መድሀኒት የሆነው
  በስሙ ሀጢአቴ ታጥቦዋል መንፈሱን ሰቶኛል
  ስሙ ይባረክ  ዳግም ተወለድኩኝ::
  3.ያ በመስቀሉ ያዳነኝ የነገስታት ንጉስ
  Beቅርብ ይመጣል አክሊል ሊያወርሰኝ
  ዥግጁ ነኝ ልቀበለው በአየር ተነጥቄ
  መቅረዜን ሳየው ያበራል ሁልጊዜ::

  4. እናንት ደካሞች ወገኖች በሀጢአት ያላችሁ
  Yeሱስ ሲገለፅ በፊቱ እንዳታፍሩ
  Meክሊታችሁን ስሩበት ለአለም አትገዙ
  ዜታ አይዘገይም አሁን ተዘጋጁ::

  5.ትኩስ ቀዝቃዛ መሆን አትመኙ
  የጌታ አገልጋይ የእሳት ነበልባል ነው
  በመንፈስ እሳት ጋላችሁ ጌታን አገልግሉ
  የሱስ ሲመለስ ክብርን እንድትለብሱ::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>በቀራኒዮ መስቀል ተሰቅሎ
  « Reply #6 on: January 02, 2012, 05:41:47 AM »

                                    2.በቀራኒዮ መስቀል ተሰቅሎ

  1.በቀራኒዮ መስቀል ተሰቅሎ
  ተሰቃየ ለሰው ልጅ ሁሉ
  እኔም አያለሁ የአምላኬን ፍቅር
  እኔን ሊያድን ክብሩን ሲጥል::

  ክብር ለእየሱሴ, ለየሱሴ, የሱሴ
  ክብር ለየሱሴ ይሁን
  በቀራኒዮ ሞቶ ላዳነኝ::

  2.ተንበርክኬ ከመስቀሉ እግር ስር ከጎኑ ምንጭ ታጥቤ ነፃሁ
  ከደዌ ሁሉ ፍፁም ዳንኩኝ
  እልል እልል ስሙ ይክበር::

  3.ሀጢአተኞች ደካሞች ሁሉ
  በመዳን ቀን ጥሪውን ስሙ
  በመስቀሉ ምንጭ ዛሬ ታጠቡ
  ከገሀነም እንድትድኑ::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>አምባ መጠጊያችን
  « Reply #7 on: January 02, 2012, 05:48:41 AM »

                                                            3. አምባ መጠጊያችን

  1.አምባ መጠጊያችን ጌታ ኢየሱስ
  የህይወት እንጀራ ነው
  ወደ እርሱ ሀጢእ ሁሉ ቢመጣ
  ከቶ ሊራብ አይችልም::

               ልረዳው ልመርምረው
               የህይወት እንጀራ ነው
              ሳይገባኝ እንዳልቀምሰው
              በሞኝነት እንዳልጠፋ::

  2.ከሰማይ የመጣ ህያው መና
  Yeኢየሱስ ስጋ ደም ነው
  Leአለም ሁሉ ህይወትን ይሰጣል
  ኧምኖ ለሚበላ ሁሉ::

  3. የሰውን ልጅ ስጋ ካልበላችሁ
  ደሙንም ካልጠጣችሁ
  በራሳችሁ ህይወት የላችሁም
  የቀራኒዮን መና ብሉ::

  4. ሀዋሪያቱ በሙሉ አጉረምርመው
  በግጣ ስጋና ደም
  ባለማወቅ እጅግ ተጨነቁ
  ማን እንደሆነ አላወቁም::


  5. ጌታ ኢየሱስ በቃሉ አፅናናቸው
  አስረዳቸው ተንትኖ
  ህይወትን የሚሰጥ መንፈስ እንጂ
  ፍጥረታዊ ስጋ አይደለም ብሎ::

  6. ሳይገባው እንጀራውን ሲበላ
  ወይም ደሙን ቢጠጣ
  የጌታ ስጋ ደም እዳ አለበት
  ሳይገባው ለሚበላው::

  7.ብዙ ግን ሳይገባችድው በልተው
  ደከሙና ታመሙ
  አያሌ ግን የቅፅበት ሞት ሞቱ
  በራሳቸው ፍርድን በሉ::

  8.እኛ ደግሞ ከጥፋት ለመዳን
  ራሳችንን እንመርምር
  ሳይገባን ስጋና ደም ወስደን
  ለዘላለም እንዳንጠፋ::

  9. ጌታ ኢየሱስ ከእራት ተነሳ
  ለማጠብ ውሀን ይዞ
  የሀዋሪያቱን እግር አጠበ
  አምላክ ነው ግን ትሁት ሆነ:.

  10. አምላክ ሽኦን እግራችሁን ካጠብኩ
  እናንተ ደግሞ አድርጉ
  ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም
  እውነት እውነት ብፁአን ናችሁ::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>ቅዱሳን ሲነጠቁ
  « Reply #8 on: January 02, 2012, 05:58:03 AM »

                                                           ቅዱሳን ሲነጠቁ

  1.     አንድ ቀን በክብር ስትመጣ
  በመላእክት ታጅበህ
  በመገለጥህ እንዳላፍር
  ጌታ ሆይ አጠንክረኝ

  ቅዱሳን ሱኢነጠቁ 2ሽ
  ጌታ ሆይ እኔም ከዚያ ልገኝ
  ቅዱሳን ሲነጠቁ::

  2.   ምናልባት ጊዜ ሳያደርሰኝ
  በአለም ስራ ተውጬ
  ፈፅሞ ስለ አንተ ሳላስብ
  ያ ቀን እንዳይመጣብኝ::

  3.   ለአንዲት ነፍስ እንኩዋን ሳልመሰክከር
     በፀሎትም ሳልተጋ
     በድንገት አንተ ብትመጣ
     ምን እሆናለሁ ጌታ

  አንተስ ክርስቲያን ወዳጄ ሆይ
  ጌታ ቢገለጥ ዛሬ
  እርሱ ከመረጣቸው ጋራ
  ለመጉዋዝ ነቅተሀል ወይ?
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>ወዳጄ ነው የሱስ
  « Reply #9 on: January 02, 2012, 06:00:06 AM »

                                              ወዳጄ ነው የሱስ

  1.   ወዳጄ ነው የሱስ ክርስቶስ
  የሁሉ ጌታና ንጉስ
  እርሱም ለእኔ ሲል ሞተልኝ
  ኸeባርነት ሊያወጣኝ::

  ሀሌሉያ ደስ ይበለን
  ለዘላለም የኢየሱስ ነኝ
  እጄን ይዞ ይመራኛል
  Weደ ሰማይ ያገባኛል::

  2.   በስልጣኑ ለዘላለም
  ይነግሳል ከሁሉ አለም
  በሀይሉ እታመናለሁ
  ከእንግዲህ ምን እፈራለሁ::

  3.   የርሱ ፍቅር ያፅናናኛል
  እረፍትንም ይሰጠኛል
  ልቤን በደስታ ይሞላልል
  መንገዴን ያቀናልኛል::

  4.   ይህ ወዳጄ ወንድሜ ሆይ
  ይጠራሀል አትሰማም ወይ
  አሁን ቅረብ አትፍራ ና
  ፀጋን ይሰጥሀልና::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>የአብርሀም አምላክ
  « Reply #10 on: January 02, 2012, 06:05:15 AM »

                           የአብርሀም አምላክ

    የአብርሀም አምላክ የይሳቅም ቤዛ 2ሽ
  ወገኖቹን ሁሉ በራሱ ደም ገዛ 2ሽ

  1.   የሀሰት ምስክር አቁመው ከሰሱት
  በሞት እንዲቀጣ ሁሉም ፈረዱበት

  2.ጲላጦስ በሰንሰለት አስሮ
  ኸeሮማዊ መንግስት እንዲኖር ተባብሮ

  3.ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ
  በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅዋ ሲንገላታ

  4.በብርሀን ዙፋን ላይ የቆሙት እግሮቹ
  Beችንካር ላይ ሆነው ምንም አልሰለቹ::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  Re: መዝሙር
  « Reply #11 on: January 02, 2012, 06:06:50 AM »

                                     ሰላም አለኝ

  1 ሰላም አለኝ 3ሽ በልቤ
  ቅዱስ ቃሉን አንብቤ
  ደህንነት አግኝቻለሁ
  ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ::

  2.   በየሱስ ደም 2ሽ ታጠበልኝ ሀጢአቴ
  ተለወጠ ህይወቴ በወንጌል እሰናለሁ
  ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ::

  3.   እረፍት አለኝ 3ሽ በኢየሱስስ
  የማይጠፋ ደስታ የማይናወጥ ተስፋ
  በህይወቴ በጣም ተስፋፋ

  4.ተለወጥኩኝ 3ሽ በኢየሱስ
  አዲስ ፍጥረት ሆኛለሁ
  መንፈሱን አግኝቻለሁ
  ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ::

  5.ሀዘን የለም ጭንቀት የለም ፍርሀት ጠፍቶዋ ከልቤ
  መንፈሱ ያፅናናኛል በደስታ ሞልቶኛል
  ጌታ ዘወትር ይጠብቀኛል::

  6.ላመስግነው 3ሽ ጌታዬን
  በመስቀል ተሰቃይቶ ከፈለልኝ እዳዬን
  ክብር 2ሽ ለስሙ ይሁን::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>ዘሩን እንሰብስብ
  « Reply #12 on: January 02, 2012, 06:08:16 AM »

                                                  ዘሩን እንሰብስብ

  1.   በጠዋት እንዝራ የደግነት ፍሬ
  በጠዋትም ሆነ በድቅድቅ ጨለማ
  መከሩን እንሰብስብ በማጨጃው ጊዜ
  በደስታ ዘሩን እንሰበስባለን::

  ዘሩን እንሰብስብ 2ሽ
  በደስታ ዘሩን እንሰበስባለን::

  2.   በፀሀይ እንዝራ በጨለማ ጊዜ
  ሰይጣንን ሳንፈራ ተከታዮቹንም
  ቀስ በቀስ ያልቃሉ ያለም ስራችንም
  በደስታ ዘሩን እንሰበስባለን::

  3.   በለቅሶ እንኩዋን ቢሆን ለጌታ እንስራ
  ብዙ ቢጠይቀን መከራም ቢበዛ
  ለቅሶዋችንም ያልቃል ከጥቂት በሁዋላ
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>እንደ ፈቃድህ
  « Reply #13 on: January 02, 2012, 06:09:43 AM »

                                        እንደ ፈቃድህ

  1.   በረሀው ሙቀቱ ውስጥ በደረቁ ስፍራ
  የሚገኙ መሀከል ቢመጣም መከራ
  ቦታው ባይስማማኝም ሰዎቹ ቢጠሉኝ
  መስቀልህን አሸክመህ የሱስ ሆይ ላከኝ

  እንደ ፈቃድህ አድርገህ እባክህ ምራኝ
  ወደፈለግሀው ቦታ አንተ ውሰደኝ
  ያሻህን እሆንልሀለሁ ተናገረኝ ጌታ
  ኢየሱሴ ውሰደኝ የትም የትም ቦታ::

  2.   ከተማም ይሁን መንደር ሰው የሚገኝበት
  ሊጠፋ የደረሰ ሀጢአት የበዛበት
  እውነቱ ያልደረሰው ጎሳ መሀከል
  ሰራተኛን ለመላክ ጌታ አስበሀልን?

  3.   አውቃለሁኝ ፈቃድህ ፍፁም አይዛባም
  የምስራቹን ሰሚ ሰውም አይታጣም
  እንዳሻህ መድሀኒቴ ብርታቱ ያንተ ነው
  Weደሚያስፈልግህ ቦታ አሽከርህን ላከው::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Onefaith
  Full Member
  ***
  Posts: 230


  View Profile Email
  መዝሙር>>እናመሰግንሀለን
  « Reply #14 on: January 02, 2012, 06:11:51 AM »

  እናመሰግንሀለን

  1.   አምላካችን ብዙ ምስጋና
  ይገባሀል ታላቅ ፍቅርን
  ለኛ ለሀጢአተኞች ብለህ
  ሰውተሀል እራሽን::

  እናመሰግንሀለን 3 ሽ
  ጌታችን መድሀኒታችን 2 ሽ

  2.   አምላካችን እንወድሀለን
  በፍቅር ለአንተ እንገዛለን
  እድሜአችንም ሁሉ ያንተ ነው
  ክብር ላንተ የቀራኒዮ ሰው::

  3.   አምላካችን የኛ መከታ
  ለዘላለም አንተን መርጠናል
  ህይወታችንንም በሙሉ
  በምስጋና ደስ ይለናል::
  Logged

  እርሱ ግን ብቻውን ነው፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው
  Pages: [1] 2 3 ... 12 Print 
  « previous next »
  Jump to:  

  HOME
  Doctrin Amharic
  Doctrin Engilish
  Tracts
  Video Youtube
  Video Prechings
  Photographs
  Audio Song
  Audio Sermon
  Amharic Bible
  English Bible
  Amharic SERA
  Amharic tracts
  English Tracts
  Amharic Articls on topic
  Articles on Topiic
  Books
  Jornals
  Forum
  Blogs
  Contact
  Help
    paltalk how
    paltalk emoji library
    Romanization converter